ድብርት (Depression)፦ ከሀዘን በላይ የሆነ የጤና ችግር
ድብርት ተራ ሀዘን ወይም የፍላጎት ማጣት ብቻ አይደለም። የሰውን ስሜት፣ አስተሳሰብ፣ እንቅልፍ፣ የምግብ ፍላጎት እና የዕለት ተዕለት ኑሮ የሚጎዳ የአእምሮ ጤና ችግር ነው።
የድብርት ምልክቶች ምንድን ናቸው?
- የማያቋርጥ ሀዘን ወይም ባዶነት መሰማት
- ቀድሞ ደስታ የሚሰጡ ነገሮች ላይ ፍላጎት ማጣት
- የእንቅልፍና የምግብ ፍላጎት መቀየር
- ድካምና የኃይል ማጣት
- ራስን መውቀስ ወይም የተስፋ መቁረጥ ስሜት
- ትኩረት ማድረግ መቸገር
ድብርት ሊታከም ይችላል!
ድብርት የባህሪ ድክመት፣ የእምነት ማነስ ወይም የፈቃድ ጉድለት አይደለም። ተገቢውን የሕክምና እርዳታ በማግኘት ሊሻሻል ይችላል።
ለሁለት ሳምንታት ወይም ከዚያ በላይ የሚቆዩ ምልክቶች ካሉዎት፣ የአእምሮ ጤና ባለሙያን ማማከር አስፈላጊ ነው።
እርዳታ መጠየቅ የድክመት ሳይሆን የድፍረት ምልክት ነው።
Yemedhnat Internal Medicine & Psychiatry Clinic



